„የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በወጣትነትህ ዘመንህ ፈጣሪህን አስብ፣ ደስ አያሰኙም የምትላቸውም ዓመታት ሳይደርሱ፣ መክብብ ምዕራፍ ፲፪ ቁጥር ፩“
በተባለው አምላካዊ ትእዛዝ መሠረት የቤተ ክርስቲያናችን አምደ ሃይማኖት የሰንበት ት/ቤት መዘምራን በሚደነቅ ሁኔታ ሁለገብ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ።
ለምሳሌ
- የአባልነት መዋጮ በመክፈል፣
- የዝማሬ አገልግሎት በመስጠት፣
- በሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤና በሕንጻ አሰሪ ኮሚቴነት በማገልገል፣
- በሰለጠነ አሰራር ለመራመድ ሙያዊ አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ እገዛ እያደረጉ ይገኛሉ።
- ለቤተ ክርስቲያናችንም የገቢ ምንጭ በማስገባት ከፍተኛውን ቦታ ይዘዋል።