ለምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ምእመናን በሙሉ በያላችሁበት

blog-img

14, März, 2020Posted by :admin(0)Comments

ጉዳዩ ፧ የኮሮና ቫይረስን ይመለከታል ።

ሰላምና ጤና  ለሁላችን እየተመኘሁ በልዩ ልዩ መገናኛ ብዙኃን  እንደምንሰማው ዓለምን ያስጨነቀው የኮረና ቫይረስ በፍጥነት እየተሰራጨ ስለሆነ  ብዙ ሕዝብ እንዳይሰበሰብ  መንግሥት ማሳሰቢያ   እየሰጠ ነው ። እንዲሁም የሀገረ ስብከታችን ሊቀ ጳጳስ የየሀገራቱ መንግሥታት የሚያወጡትን መመሪያ ተከትሎ ተግባራዊ ማደረግ እንደሚገባ መመሪያ ሰጥተዋል ። በመሆኑም

፩ኛ . ለነገ የተጠራው ዓመታዊ የአባላት ስብሰባ የቀረ መሆኑን ፣

፪ኛ . ችግሩ ተወግዶ መልካም ዜና እስኪሰማ ድረስ  በየቤታችን  ፈጣሪን በጸሎትና በምህላ እንድንጠይቅ ፣ 

፫ኛ . የባንኩ እዳ በየወሩ ሳይቋረጥ ሲከፈል የነበረው ከሙዳየ በረከት ፣ ከሰንበት ምሳና ከልዩ ልዩ በሚገኝ ገቢ /ርዳታ ጭምር እንደነበር ግልጽ ነው ።

ስለዚህ በየወሩ ለባንክ የምንከፍለው ጎድሎ  ቤተ ክርስቲያናችን ችግር ላይ እንዳይወድቅ በየሰንበቱ ስናደርግ የነበረውን አስተዋጽዖ  አጠራቅመን በባንክ ወይም ችግሩ ሲወገድ በገንዘብ ቤት በኩል በእጅ የተለመደውን ሳምንታዊ ርዳታ እንድናደርግ በታላቅ አክብሮት እናሳስባለን ።

ፈጣሪ ቸር ዜና ያሰማን።

መልአከ መዊዕ ልሳነወርቅ ውቤ

የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ

Leave Comments