ጉዳዩ ፧ የኮሮና ቫይረስን ይመለከታል ።
ሰላምና ጤና ለሁላችን እየተመኘሁ በልዩ ልዩ መገናኛ ብዙኃን እንደምንሰማው ዓለምን ያስጨነቀው የኮረና ቫይረስ በፍጥነት እየተሰራጨ ስለሆነ ብዙ ሕዝብ እንዳይሰበሰብ መንግሥት ማሳሰቢያ እየሰጠ ነው ። እንዲሁም የሀገረ ስብከታችን ሊቀ ጳጳስ የየሀገራቱ መንግሥታት የሚያወጡትን መመሪያ ተከትሎ ተግባራዊ ማደረግ እንደሚገባ መመሪያ ሰጥተዋል ። በመሆኑም
፩ኛ . ለነገ የተጠራው ዓመታዊ የአባላት ስብሰባ የቀረ መሆኑን ፣
፪ኛ . ችግሩ ተወግዶ መልካም ዜና እስኪሰማ ድረስ በየቤታችን ፈጣሪን በጸሎትና በምህላ እንድንጠይቅ ፣
፫ኛ . የባንኩ እዳ በየወሩ ሳይቋረጥ ሲከፈል የነበረው ከሙዳየ በረከት ፣ ከሰንበት ምሳና ከልዩ ልዩ በሚገኝ ገቢ /ርዳታ ጭምር እንደነበር ግልጽ ነው ።
ስለዚህ በየወሩ ለባንክ የምንከፍለው ጎድሎ ቤተ ክርስቲያናችን ችግር ላይ እንዳይወድቅ በየሰንበቱ ስናደርግ የነበረውን አስተዋጽዖ አጠራቅመን በባንክ ወይም ችግሩ ሲወገድ በገንዘብ ቤት በኩል በእጅ የተለመደውን ሳምንታዊ ርዳታ እንድናደርግ በታላቅ አክብሮት እናሳስባለን ።
ፈጣሪ ቸር ዜና ያሰማን።
መልአከ መዊዕ ልሳነወርቅ ውቤ
የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ