ሁለተኛ የአባላት መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ

blog-img

06, März, 2023Posted by :admin(0)Comments

ለምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን አባላት በያላችሁበት

የጠቅላላ አባላት ዓመታዊ ስብሰባ ጥሪ

ለ05.03.2023 የተጠራው መደበኛ ጠቅላላ የአባላት ስብሰባ ምልዓተ ጉባኤ ባለመሟላቱ ሁለተኛውን የአባላት መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በ07.05.2023 ከጧቱ 11.00 ሰዓት ጀምሮ በቤተ ክርስቲያናችን ከቅዳሴ በኋላ ስለምናካሂድ  በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት እንዲገኙልን በአክብሮት እንጠይቃለን ::

የመነጋገሪያ አጀንዳዎች:

፩   የመክፈቻና እንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት በሰብሳቢው፣

፪   ዓመታዊ የሥራ ሪፖርት

፫   የኦዲትና ሂሳብ ሪፖርት ናቸው፡፡

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ቤተ ክርስቲያናችን ይባርክልን፣ይጠብቅልን!

ለመላው ዓለምም ሰላምን ይስጥልን አሜን::              

ማሳሰቢያ:

የአባልነት ክፍያ ውዝፍ ካለብዎ ከሂሳብ ክፍል ጋር በመነጋገር ከስብሰባው ቀን በፊት እንዲያጠናቅቁ በአክብሮት እያሳሰብን የእርስዎም በስብሰባው ላይ መገኘት የአባልነት መብትና ግዴታዎ መሆኑን እንገልጻለን:


የቤተ ክርስቲያኑ ሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ጽ/ቤት

Leave Comments